ስለ እኛ የተቋሙ ራእይ በ2022 ዓ.ም የአምራች ኢንዱስትሪዉ ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳር ሆኖ ማየት የተቋሙ ተልእኮ አሰራርን ግልፅ፣ ተደራሽና ውድድር የሰፈነበት እንዲሆን በማድረግ፣ ለባለሃብቱ የላቀ አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት፤ የዘርፉን የሰው ሀብትና የቴክኖሎጂ አቅም በማሳደግ እና ውጤታማ የአሠራር ስርዓት በመዘርጋት የአምራች ኢንዱስትሪውን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ፡፡ የተቋሙ ዋና ዋና የትኩረት መስኮች ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ማጎልበትየአምራች ኢንዱስትሪ የግብዓት አቅርቦትና የማምረት አቅም አጠቃቀም ማሳደግየአምራች ኢንዱስትሪ የወጪ እና ተኪ ምርት ማሳደግየአምራች ኢንዱስትሪ ኢንቨስትመንት መሳብና የሥራ ዕድል ማሳደግየአምራች ኢንዱስትሪ ምርምርና ስርጸት አቅምና ዉጤታማነት ማሳደግ