የቢሮ ኃላፊ መልዕክት

አቶ አሻግሬ ጀንበሬ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ
እንደ ሀገር ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰሩ ያሉ እና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማስመዝገብ የብዝኃ ኢኮኖሚ ዘርፎች ናቸው ተብለዉ ከተለዩ ዘርፎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ አንዱ ሲሆን፡ ይህንን እውን ለማድረግ እንደ ሀገር የአምራች ኢንዱስትሪ ፓሊስና ልዩ ልዩ ስትራቴጂዎችን በማውጣት ተግባራዊ ማድረግ ተችሎአል ፡፡
ከዚህ በፊት በሚዛኑ ትኩረት ያላገኙ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ባለሀብቶች በዘርፉ እንዲሰማሩ ማድረግ እና በተመሳሳይ በሀገር ውስጥ ተመርተዉ ወደ ውጪ የሚላኩ ምርቶች እና በሀገር ውስጥ ተመርተዉ በሀገር ውስጥ የመጠቀም ባህል ማሳደግ ተችሎአል ፡፡
በሲዳማ ክልል አምራች ኢንዱስትሪን ለማጠናከር እና ለማስፋፋት የፌደራልና የክልሉ መንግስት በቅንጅት የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ የቆዬ ሲሆን ከእነዚህም ተግባራቶች ውስጥ :-
ልዩ የኢኮኖም ዞን ማቋቋም (የሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ): የተቀናጀ የግብርና ምርት ማቀነባበሪያ ፓርክ ማቋቋም፤ መሬትና መሰረተ ልማቶችን ማመቻቸት፤ የፋይናንስ ተቋማትን ማቋቋም፤ ስራ ፈላጊዎችን የሚያሰለጥኑ ዩንቨርስቲና የቴክንክና ሙያ ኮሌጆችን ወደ ስራ በማስገባት፤ ከሀዋሳ ዩንቨሪሲት ጋር በመተባበር የአምራች ኢንዱስትሪ ፍኖተ ካርታ፤ ስትራቴጅክ ዕቅድ ጥናቶች የተጠናቀቁ ሲሆን በተጨማሪ የክልሉን አቅም የሚያሳይ ጥናት በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል፡፡
በቴክኖሎጅ የተደገፉ የአንድ ማዕከል አገልግሎቶችን ወደ ሰራ ማስገባት የተቻለ ሲሆን፤ በሲዳማ ክልል በተለያዩ አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሰማራት ምቹ ሁኔታ ያለ በመሆኑ በሀገር ውስጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ የምትገኙ ባለሀብቶች በክልሉ ውስጥ በሚገኙ ኢንዱስትሪ ፓርኮችና ከፖርክ ውጪ መዋለ ነዋያችሁን በማፍሰስ እራሳችሁን እና ሀገራችሁን እንድትጠቅሙ የቢሮ ሀላፊው ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡