sbid

በአምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የኢንዱስትሪ ምክር ካውንስል ሚናው ከፍተኛ ነው። አቶ ተሰማ ዲማ

የካቲት 12/2018 የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት

በክልሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የኢንዱስትሪ ምክር ካውንስል ጥናት በማድረግ ውጤታማ ስራ እየሰራ መሆኑን የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ እና የኢንዱስትሪ ካውንስሉ ሰብሳብ አቶ ተሰማ ዲማ ተናግረዋል።

የክልል ኢንዱስትሪ ልማት ካውንስል ቴክኒክ ኮሚቴ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት ባለድርሻ አካላት በታደሙበት ገምግሟል።

በመድረኩ ተገኝተው በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ፕሬዚዳንት አማካሪ እና የኢንዱስትሪ ምክር ካውንስሉ ሰብሳብ አቶ ተሰማ ዲማ እንደተናገሩት ካውንስሉ በየጊዜው አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያነሱትን ቅሬታና ማነቆዎች ጥናት በማድረግ እንደየባህራቸው በወቅቱ ለመፍታት እየሰራ መሆኑን ተናግሯል።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በበኩላቸው አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያቀርቡትን ጥያቄዎች በወቅቱ ለመፍታት ካውንስሉ አስፈላጊውን ጥናት በማድረግ የዘርፉን እድገት ለማፋጠን ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ መሆኑን አንስተዋል።

የቴክኒክ ኮሚቴ ሪፖርት ያቀረቡት የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ እና የቴክኒክ ኮሚቴው ስብሳቢው አቶ ሻሻሞ ቂልሳ በተደረገው ጥናት የአምራች ኢንዱስትሪዎች ችግር የገበያ ትስስር፣ የመብራት መቆራረጥ ፤የማስፋፊያ ቦታ፣የብድር አቅርቦት ፤የካፒታል ችግርና የመሰሳሰሉት መሆናቸው ለካውንሉ አቅርቧል።

በመጨረሻም በመድረኩ ሁሉም ባለድሻ አካላት የታደሙ ስሆን በየዘርፉ የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ ያቀረበው ጥናት እንደአስፈላጊነቱ ተቋማቶች ተቀናጅተው ለመፍታት ሰፊ ውይይት አድርጓል።

Scroll to Top