የተገልጋይ እርካታ ለማረጋገጥ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል:-አቶ አሻግሬ ጀንበሬ
መጋቢት 30/2018 ዓ.ም ሲዳማ ክልል ኢንዱሰትሪ ልማት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሮክቶሬት
የተገልጋይ እርካታ ለማረጋገጥ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል ስሉ የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ ተናግረዋል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በዛሬው ዕለት የሪፎርም ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ለቢሮ አመራርና ለሠራተኞች ጋር እየተካሄደ ነው።
በውይይቱ መድረክ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በሁሉም የስራ ዘርፍ ለተገልጋዮች ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ያስፈልጋል እንዲሁም የተሰጠንን ስራ በታማኝነት በመወጣት እንግልትን በመቀነስ ሰዓት ማክበርና ስራ በአግባቡ መጨረስ ባህላችን ልሆን ይገባል ብለዋል።
በመቀጠልም በበጀት አመቱ የተጀመሩ ስራዎች በታቀደላቸው እቅድ መሠረት ማጠናቀቅ እንዲሁም በቀሩት ጊዜያት በጥንካሬ እና በጉድለት የተለዩ ስራዎችን ሠራተኞች በታማኝነት መጨረስና ጥሩ ውጤት ማስመዝገብ ያስፈልጋል በማለት መልዕክት አስተላልፏል።
በመጨረሻም ቢሮው የሪፎርም ስራዎች ላይ ያተኮረ ውይይት ለአመራርና ለሠራተኞች ጋር እየተካሄደ ይገኛል ።