sbid

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አመራርና ባለሙያዎች በይርጋለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ መድረክ አካሄዱ

በመድረኩ የቢሮው የ2017 ዕቅድ ክንውን፣ የ2018 በጀት አመት ዕቅድ ከዚህ የተቀዳ የቀጣይ 90 ቀናት ዕቅድ እና የ2018 በጀት ዓመት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ቀርቦ የቢሮው ኃላፊዎች እና ሠራተኞች ጋር ውይይት አድርገዋል።

‎በመድረኩ የቢሮው ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና የመክፈቻ ንግግር ስያደርጉ በ2017 በዓመቱ መጀመሪያ ለቢሮ የተሰጠውን ተልዕኮ መሠረት በማድረግ የተቋም ግንባታና ስትራቴጅክ ግቦችን ለማሳካት ታቅዶ ወደ ስራ መገባቱን በመግለጽ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ አመራሩ፣ባለሙያዎች እና ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተን በሰራነው ስራ የተሻለ ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።

‎ኃላፊው አቶ ጎሳዬ አያይዘውም በ2017 በጀት ዓመት የተከናወኑ ስኬቶቻችን በልዩ ጥንካሬ ለማስቀጠል እና በሂደቱ የተለዩ ደካማ አፈጻጸም በ2018 በጀት ዓመት ለመካስ በቢሮ የተጀመረውን ተቋማዊ ለውጥ እስከ ታችኛው መዋቅር በማጠናከር በዋና ዋና ስትራቴጂካዊ ግቦቻችንን በማትኮር ወደ ስራ መግባት ይገባናል ብለዋል።

‎በመቀጠልም የቢሮው የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ከዚህ ቀደም በተመዘገቡ ጠንካራ አፈጻጸም ውጤቶች ሳይዘናጉ በቀጣይ በ2018 በጀት አመት የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ መጣር እንደሚገባቸው አቶ ጎሳዬ አሳስበዋል።

‎የቢሮ ኃላፊዎችና ባለሙያዎችም በ2018 በጀት አመት ከወትሮው የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ እና የህብረተሰቡን ተጠቃምነት ለማረጋገጥ ጠንክረው ለመስራት ያላቸውን አቋም በአስተያየታቸው ገልጸዋል።

ሐምሌ 20/2017 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Scroll to Top