የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ የሚመራው ልዑካን ቡድን በክልሉ ስራ ውስጥ የገቡ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን በተለየዩ አከባቢዎች ጉብኝት ማድረግ ጀምረዋል።
ጥር 26/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት
በበጀት አመቱ የስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም በማስመልከት የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እንዳስታወቀው 120 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን የተነገረ ስሆን
በሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ የሚመራው የቋም ኮሚቴው ልዑካን ቡድን በሀዋሳና ይርጋዓለም ጉብኝት በማድረግ ላይ ነው።
በጉብኝቱ ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ፣ የምክር ቤቱ ምክትል አፈጉባኤ ክቡር አቶ ዘነበ ዘርፉ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበር እና የምክር ቤቱ ቋም ኮሚቴዎችና የቢሮ አመራሮች ተገኝተዋል።