ያደጉ ሀገሮች የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር መሰረታቸው አምራች ኢንዱስትሪው ነው አቶ አሻግሬ ጀንበሬ።
የካቲት 9/2018 የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት
ያደጉ ሀገሮች የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር መሰረታቸው አምራች ኢንዱስትሪው ነው ስሉ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ ተናግረዋል።
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ”ኢንዱስትሪያላይዜሽን ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር” በሚል መሪ ቃል ”የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወር አፈጻጸም ግብረ-መልስና ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ላይ የውይይት መድረክ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ከተማ በማካሄድ ላይ ይገኛል።
በመድረኩ ተገኝተው በይፋ ያስጀመሩት የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ እንደተናገሩት በክልሉ ባለፉት ወራት የኢንዱስትሪ ዘርፍን ለማነቃቃት ዘርፈብዙ ስራ በመሰራቱ ትልቅ ውጤት መገኘቱን ተናግረው በአለማችን የትኛውም ሀገር ያለኢንዱስትሪ እድገት ያሳዬ የለም በመሆኑም ኢንዱስትሪ የሕብረተሰብን ኑሮ ለማሻሻልና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳለጥ ወሳኝ ነው በማለት ተናግረዋል።
የደቡባዊ ሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ መንገሻ ፊታሞ በውይይቱ ላይ እንደገለፁት ሀገራችን የያዘችውን እቅድ ከዳር ለማድረስ መንግሥት ቁርጠኛ አቋም ይዘው እየሰራ በመሆኑ በክልላችንም ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት የተጀመሩ ስራዎች ውጤታማ ናቸው ብለዋል።
በመጨረሻም የስድስት ወራት የስራ እቅድ አፈጻጸምና የግብረ-መልስ መድረክ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የተገኙበት እና የተለዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖች በመለየት በአመቱ መጨረሻ የተያዘውን እቅድ መሉ በሙሉ ለመፈጸም ይሰራል ተብሏል።