አምራች ኢንዱስትሪዎች በዘርፉ ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያስመዘገቡ ነው አቶ አሻግሬ ጀንበሬ።
የካቲት 10/2018 የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች አምራች ኢንዱስትሪዎች በዘርፉ ለሕብረተሰቡና ለአገር ትልቅ ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን እያስመዘገቡ ነው ስሉ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሮ ጀንበሬ አስታወቀ።
በየዞኖቹ የተጀመረው ውይይት ዛሬም የቀጠለ ስሆን ምስራቃዊ ሲዳማ ዞንና ማዕከላዊ የሲዳማ ዞን አስተዳደር አስተዳዳሪዎች፣ የወረዳዎች አስተዳዳሪዎችና አስፈጻሚ እንድሁም የዘርፉ አመራር በታደሙበት በሀዋሳ ከተማ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም እና የግብረመልስ ውይይት ተደርጓል።
መድረኩን በይፋ ያስጀመሩት የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ እንደተናገሩት በዚህ በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት ዋና ዋና በሆኑ የተኪ ምርት፣ የማምረት አቅም አጠቃቀም ፣የግብዓት አቅርቦት፣ለሥራ ዕድል ፈጠራ፣አዳዲስ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር፣ነባር እንዱስትሪ ለማጠናከርና ሌሎች የዘርፉ ስራዎች ተስፋ ሰጪ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጿል።
የምስራቃዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳደር አቶ ግዛቸው ኖኦራ እንደተናገሩት የሀገርን ኢኮኖሚ ለማሳደግ በሚደረገው አስተዋፅኦ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ሚና ከፍተኛ በመሆኑ የግብዓት አቅርቦት ትስስር በመፍጠር ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የግብዓት አቅርቦት ማነቆዎችን በመፍታት የምርትና ምርታማነትን እድገት ማሳደግ እንደሚገባ ተናግረዋል።
የማዕከላዊ ሲዳማ ዞን አስተዳዳሪ አቶ መንግሥቱ በቀለ እንደተናገሩት ተኪ ምርት እና ኤክስፖርት የሚያደርጉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማጠናከር ለማክሮ ኢኮኖሚ ያላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል።
በመጨረሻም የኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማነቃቃት እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ለማበረታታት ሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ዘርፍን ለማስፋፋትና ለማሳደግ የድርሻችንን እንወጣ መልዕክትም አስተላልፏል።