sbid

የኢንዱስትሮች ማምረት አቅሙን 85% ለማድረስ እየተሠራ እንደሚገኝ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ገለፀ።

የካቲት 19/2018 ዓ.ም ሲዳማ ክልል መንግስት ኮሙኒኬሽን ቢሮ

ቢሮው ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ኢንዱስትሪዎችን የመፍጠር ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የቢሮ ምክትልና ኢንዱስትሪ ማስፋፍያ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሻሻሞ ቂልሳ እንደገለፁት፣ በክልሉ 1ሺህ 455 የሚሆኑ አምራች ኢንዱስትሪዎች መኖራቸውን ተናግረው 87 ኢንዱስትሪዎች ደግሞ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን የመተካት እና ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶችን በማምረት የውጭ ምንዛሬውን በማስቀረት ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።

በክልል ደረጃ በ2014 ዓ.ም የኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸው 44% ከነበረበት የክልሉ መንግስት ከጊዜ ወደ ጊዜ ባደረገው ክትትልና ድጋፍ በአሁኑ ወቅት 63% ከፍ ማለቱን የጠቆሙት ኃላፊው በሚቀጥሉት 5 አመታት ወደ 85% ለማድረስ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል።

ቢሮው አምራች ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት አሁን የተፈጠረውን የሥራ እድል ለመጨመር አቅዶ እየሠራ እንደሚገኝ አመላክቷል።

አበራ አብርሃም ፈርንቸር፣ሪቨርስ ኢንጂነሪንግ እና ከብሮን የተራዞ ማምረቻ ኢንዱስትሪዎች ተተኪ ምርቶችንና ወደ ውጭ የሚላኩትን ከሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው። የሦስቱም ኢንዱስትሪዎች ሥራ አስኪያጆች እንደገለፁት፣መንግስት ክትትልና ድጋፍ ከማድረጉ ጎን ለጎን የማምረቻና የመሸጫ ቦታዎቹን በመስጠት እንዲደግፋቸው ጠይቀዋል።

ለኢንዱስትሪዎች የገቢያ ትስስር ከመፍጠር እና የመሥሪያ ቦታዎች ጥበት ችግሮችን ከመፍታት ረገድ ቢሮው ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሠራ እንደሚገኝ የቢሮ ምክትል ኃላፊ አስገንዝበዋል።

Scroll to Top