ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ "ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ ታምርት" በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ የተዘጋጀውን የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽን እና ባዛር በይፋ ከፈቱ
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ “ለኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ኢትዮጵያ ታምርት” በሚል መሪ ቃል በሀዋሳ ሚሊኒየም አደባባይ የተዘጋጀውን የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቢሽን እና ባዛር በይፋ ከፍተዋል።
በአምራች ኢንዱስትሪዎች የቀረቡ ምርቶችን ተዘዋዉረው የተመለከቱት ርዕሰ መስተዳድሩ አምራቾችን እና የፈጠራ ባለቤቶችን አበረታተዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪዎች ኤግዚቪሽን እና ባዛር ለቀጣይ አምስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
በሀዋሳ እና አካባቢዋ የሚገኘው ሸማቹ ህብረተሰብ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በመሸመት እንዲጠቀም ጥሪ ቀርቧል።