ባለፉት 5 አመታት በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
ሀዋሳ|መጋቢት 25/2018 ዓ.ም
ሲዳማ ክልል ኢንዱሰትሪ ልማት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ዳይሮክቶሬት
በሲዳማ ክልል ባለፉት 5 አመታት በኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን ተነግሯል።
ለአገር ኢኮኖሚ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የጀርባ አጥንት በመሆኑ አገራዊ ለውጥን ተከትሎ በክልሉ በተሰጠው ትኩረት ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገብ ተችሏል።
በክልሉ የኢንዱስትሪ ማስፋፋት እና የውጭ ምርቶችን በሀገር ውስጥ የመተካት ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ በማስገባት ለሕብረተሰቡ ችግር ፌች በሆኑ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ጎን ለጎን ለአከባቢው ማህበረሰብ ደግሞ ጊዜያዊና ቋሚ የስራ ዕድል አማራጮች መፍጠር ችሏል።
የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አምራች ኢንዱስትሪዎችን በመደገፍ፣ በማማከርና በማሰልጠን የሚያጋጥሙ ችግሮችን ከስርስር በመፍታት በዘርፉ ላይ የተሰማሩ በየጊዜው አመርቂ ውጤት እያስመዘገቡ መሆናቸውን ተመላክተዋል።