sbid

አምራች ኢንዱስትሪዎች የሕብረተሰብን ኑሮ ጫና ለማቃለል ውጤታማ ሰራዎች እየተሰሩ ነው፦ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ

ጥር 26/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት

በክልሉ በተለያዩ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሕብረተሰቡን የኑሮ ጫና ለማቃለል ውጤታማ ስራዎችን እየሰሩ ነው ስሉ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ ተናገሩ።

በክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብሪት ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ የሚመራው ልዑካን ቡድን በሀዋሳና በይርጋዓለም ስራ ውስጥ የገቡ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ተዘዋውረው ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ መርሐግብር ላይ የሲዳማ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንታዬ እንደተናገሩት በክልሉ ስራ ፈላጊ ሳይሆን ስራ ፈጣሪ ወጣት ለማብዛት እየተሰራ በመሆኑ በአከባቢው ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከፍ የሚያደርግ እና ለብዙ ዜጎች ስራ በሚፈጥር መልኩ ኢንዱስትሪዎችን ለማስፋፋት በተሰራው ስራ ትልቅ ውጤት መመዝገቡንና አምራች ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ መሆናቸውን ተናግሯል።

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ እንደተናገሩት በበጀት ዓመቱ የስድስት ወር የስራ አፈጻጸም 120 አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ስራ ማስጀመራቸው እና በዚህም ለ9 ሺህ ሰዎች ስራ መፈጠሩን እንዲሁም 50 ሚሊዮን ዶላር የሚሆን ምርት ወደ ውጪ ኤክስፖርት መደረጉን ፣ 137.6 ሚሊዮን ዶላር ተኪ ምርት መመረቱን እና የኢንዱስትሪዎች ምርታማነት 63.5% መድረሱን ተናግረዋል።

በመቀጠልም በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ የገጠር ኢንዱስትራላይዜሽንን ማስፋትና ተጨማሪ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ ማስገባት፣ በተለያዩ ምክንያት ስራ ያቆሙትን በማስጀመር እንደሁም አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርታማነት ከፍ እንዲል በማድረግ ለ27 ሺህ ዘጎች ቀጥተኛ የስራ ዕድል ለመፍጠር እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዛሬው ዕለት ጉብኝት የተደረጉ የSDC የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ ደብሊው ኤም ኢንጂነሪንግ፣ ጽሩይ ሳሙናና ዲተርጀንት ፋብሪካ፣ ከድጃ ዱቄት ፋብሪካ ፤ኢንጅነር ዘላለም ወ/አማኑኤል ጎልደን አቮካዶ የተፈጥሮ ዘይት ማምረቻ ፋብሪካ፣Mei Mei የቡና ማቀነባበሪያና ሌሎች የተጎበኙ ስሆን በስራ ውጤታማነት እና ተግዳሮቶች ላይ ሰፍ ውይይት ተደርጓል።

Scroll to Top