"ውጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር" በሚል ርዕሰ ላይ በክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለፓርቲ አባላት ሥልጠና ተሰጠ ።
የካቲት 05/2018 የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት
7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ፣ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ እንድሆን “ውጤታማ ምርጫ ለተምሳሌት ሀገር” በሚል ርዕሰ ላይ በሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ለብልፅግና ፓርቲ አባላት ሥልጠና ተሰጥቷል።
በስልጠናው መድረክ ላይ የቢሮ ምክትል ሀላፊና ኢንዱሰትሪ ዘርፍ ሀላፊ አቶ ሻሻሞ ቂልሳ እና የቢሮ ምክትል ሀላፊ እና የፋይናንስ የአስተዳደር ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተስፋዬ ቱንጋሞ እንደተናገሩት 7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ውጤታማ እንድሆን ብልጽግና ፓርቲ ሁለት ዋና ዋና ግቦችን መያዙን ገልጾ፣
በተጨማሪ ምርጫው እጅግ ሰላማዊ ነፃ፣ፍትሐዊና ተአማኒ በማድረግ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታውን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር ምርጫውን በአሸናፊነት በማጠናቀቅ፣ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ቅቡልነት ያለው መንግስት መመሥረት የጀመርናቸውን የብልፅግና ጉዞ እንደሚፋጠን ገልጿል።
በተጨማሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከስልጣን ፉክክር ባለፈ ኢትዮጵያ ለጀመረችው የሀገር መንግስት ግንባታና ለዲሞክራሲያዊ ሽግግር ስኬታማ እንድሆን ምናቸው እንድወጡ በማለት ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።
በመጨረሻም የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ በሰላማዊ መንገድ እንዲካሄድ የቢሮ ሠራተኞች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስቧል።