በሲዳማ ክልል የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች አበረታች ውጤት እያስመዘገቡ ነው አቶ መላኩ አለበል ።
በሲዳማ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ ኢንዱስትሪዎች ለአገርቷ ኢኮኖሚ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ ነው ስሉ የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለበል ተናግሯል።
የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ምንስቴር በዛሬው ዕለት ሲዳማ መዲና ሀዋሳ በመገኘት ሱፐር ኦቫ አግሮ ቴክ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ, ልዩ የኢኮኖሚ ዞን እና በይርጋዓለም የተቀናጀ የግብርና አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በመገኘት በክልሉ ባለድርሻ አካላት ጋር ጉብኝት አድረገዋል።
በጉብኝቱ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለበል ኢንዱስትሪዎቹ የአገራችን ኢኮኖሚ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና ስላላቸው በጉብኝቱ ምዕራፍ ላይ ያየነው ሀዋሳ ሱፐር ኦቫ አግሮ ቴክ የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ፣ ሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ውስጥ ቶዮ ካምፓን እና የይርጋአለም የተቀናጀ አግሮ ኢንዱስትሪ ከአከባቢው አልፎ ለአገር እድገት ተስፋ ናቸው በማለት ተናግረዋል።
የክልሉ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና እንደተናገሩት ዘርፉን የበለጠ ለማሳደግ በተሰራው ስራ በሲዳማ ክልል ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ተናግሮ፣ አገራችን የነደፈችውን የእድገት እቅድ ለማሳካት የኢንደስትሪ ዘርፍ ሚናው ከፍ ያለ በመሆኑ ተጨባጭ ለውጦች እየተመዘገቡ ናቸው በማለት ተናግረዋል።
በጉብኝቱ መርሐ ግብር ላይ የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ምንስቴር ምንስትር አቶ መላኩ አለቤል፣ ምንስቴር ዴታ አቶ ሀሰን መሀመድ ፣ አቶ ታረቀኝ በሉልታ, የክልሉ የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ተጨምሮ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር ጉብኝት ተደርጓል ።
ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት