sbid

በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር) የተመራ ቡድን የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክን ጎብኝቷል።

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ቦርድ አባል አቶ ጎሳዬ ጎዳና በስፍራው ተገኝተው በክልሉ የኢንዱስትሪው ዘርፍ እያደገ መምጣቱንና የይርጋለም የተቀናጀ የግብርና ኢንዱስትሪ ፓርክም የዚሁ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ የተራ በበኩላቸው፥ የፓርኩን የስራ እንቅስቃሴና ያሉትን መልካም እድሎች የሚገልጽ ፅሁፍ አቅርበው ለቡድኑ ገለጻ አድርገዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው እንደገለጹት የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶችን ለመሳብ በተሰራው የፕሮሞሽን ስራ የአልሚ ባለሀብቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል፤ በዚህም ለበርካታ ዜጎች ስራ ዕድል ከመፍጠርም በላይ የውጪ ምንዛሪ እየተገኘ መሆኑንም ገልፀዋል።

በመጨረሻም ቡድኑ ፓርኩ ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎችን የስራ እንቅስቃሴ ከጎበኙ በበኋላ በፓርኩ ያዩት ተጨባጭ ነገር ተሰፋ ሰጪ መሆኑንና በቀጣይ ከሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ጋር በቁርኝት እንደሚሰራም ተወያይተዋል።

Scroll to Top