የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት አመት መሪ ማስፈፀሚያ ዕቅድ ላይ የውይይት መድረክ እየተከናወነ ነዉ
ኤክስፖርት መር ተወዳዳሪ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬን ለመሳብ ጠንክረን እንሰራለን-አቶ አስፋው ጎኔሶ
ቢሮው ከ2014 በጀት አመት ጀምሮ በተሻለ አፈጻጸም ባስመዘገበው አመርቂ ውጤት ለአራት ተከታታይ አመታት በሀገር ደረጃ ለእውቅናና ሽልማት በቅቷል።
በብልጽግና ፓርቲ ሲዳማ ክልል ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ፓለቲካና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አስፋው ጎኔሶ በመድረኩ መክፈቻ ንግግር ሲያደርጉ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት አመት ጨምሮ ባለፉት አራት አመታት በአፈጻጸም በሀገር ደረጃ ግንባር ቀደም መሆኑን ጠቁመው፣በዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰሩ ስራዎችን ጠንክሮ በመስራት ረገድ በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ አመራርና ባለሙያ በቀጣይም በጋራ ተቀናጅተው ለተሻለ አፈጻጸም መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
አቶ አስፋው አያይዘውም በሚቀጥለው ጊዜ አምራች ኢንዱስትሪዎች ጥራቱን የጠበቁ ምርቶችን በማምረት የውጪ ምንዛሬ በማስገኘት፣ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር በቀል ምርቶች በመተካት እንዲሁም ዘርፉ ከሌሎች ከግብርና፣ንግድና ኢንቨስትመንት ጋር ጠንካራ ትስስር ፈጥሮ በመስራት የላቀ ውጤት እንዲያስመዘገብ የዘርፉ አመራርና ባለሙያዎች በጥንካሬ እንዲፈጽሙ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና በ2017 በጀት አመት ተቋሙን ለመገንባትና በዘርፉ አምስት ስትራቴጂክ ግቦች ልዩ ትኩረት ሰጥተን በሂደቱም በኢንዱስትሪ ዘርፍ ኢኮኖሚ ሽግግር ለማረጋገጥና ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር በተሰሩ ስራዎች የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በአምናው አፈጻጸም የተሻለ ውጤት አስመዝግበን ለእውቅናና ሽልማት በቅተናል ብለዋል።
አቶ ጎሳዬ አክለውም ባለፉት አመታት ያስመዘገብነው ውጤት እንደተጠበቀ ሆኖ በሚቀጥለው 2018 በጀት አመት በአፈጻጸም ያሳየንን ጠንካራ ጎናችን አጠናክረን በማስቀጠል በክልሉ ያለውን ዘርፈ ብዙ ምቹ ሁኔታዎችን በሙሉ አሟጠን በመጠቀም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት መፈጸም ይጠበቅብናል ብለዋል።
ቢሮው በ2017 በጀት አመት በመደበኛ ስራዎች አፈፃፀም የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ከአንድኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃን ለያዙ ዞኖች፣የቢሮው ዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች እውቅናና ሽልማት ተሰጥቶ መድረኩ የሚጠናቀቅ ይሆናል።
ነሐሴ 09/2017 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት