የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአገልግሎት አሰጣጥ እና ተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ
የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚ ኮሌጅ ጋር በመተባበር በአገልግሎት አሰጣጥ እና ተገልጋይ እርካታ ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ የሚያስችላቸውን የጋራ ስምምነት በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል።
በመድረኩ ላይ በመገኘት የፊርማ መርሀ_ግብሩን ያስጀመሩት የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፍ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ቢሮው ህብረተሰቡን ተጠቃም የሚያደረጉ የተለያዩ የልማትና ሰው ተኮረ ስራዎችን ከመስራትም ባለፉ ዓመታት ውጤታማ መሆኑን አንስተው የህብረተሰቡን የልማትት ፍላጎት ጊዜው በሚጠይቀዉ ሁነታ ለመመለስ የተገልጋይ ዕርካታ ያለበትን ደረጃ ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መለየትና በጥናቱ መነሻ የማሻሻያ ስራዎችን መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል ።
ጥናቱ ጥራቱን ጠብቆ በተያዘለት ጊዜ እንድጠናቀቅ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ጥርያቸውን አቅርበዋል ።
በጋራ ስምምነት መድረኩ ላይ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና ፣ የቢሮው ማናጅመንት አባላት አንዲሁም የአዋዳ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮለጅ አጥኚ ቡድን አባላት ተገኝተዋል ።
ሀዋሳ|| ነሐሴ 20/2017 ዓ.ም ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት