sbid

ከውጪ የሚገቡ ማሽኖችን በክልል ውስጥ ለማምረት በተደረገው እንቅስቃሴ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ ነው አቶ ጎሳዬ ጎዳና።

በአቶ ጎሳዬ ጎዳና የተመራው ልዑካን ቡድኑ በሀዋሳ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ማሽን አምራች ኢንዱስትሪዎችን ጉብኝት በማድረግ ላይ ይገኛል ።

በጉብኝቱ መርሐ_ግብር ላይ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና እንደተናገሩት ከዚህ ቀደም የተለያዩ ማሽኖች በውጪ ሚንዛሪ ከውጪ እንደሚገቡና መንግስት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በክልል ውስጥ በማምረት ለተጠቃሚዎች ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን እና ይህ ተግባር ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ በተጨማር ዘርፈ ብዙ ፍይዳ እንዳለው ሀላፍው የገለፁ ስሆን

በክልሉ እየተመረቱ ከምገኙ ማሽኖች እና አካላት መካከል ውስጥ የመኪና እና ሞቴርሳይክል መለዋዎጫ፣የእንሰሳት የመኖ ማቀነባበሪያ ማሽን፤የሳሙና ማምረቻ፣ፒላስቲክ መልሶ ለመጠቀም የምያገለግሉ ፤ለሀገራዊ ጫካ ፐሮጀክት እና በክልሉ ለምገነቡ መንገዶች የምያገለግሉ ተንጠልጣይ ድልድይ ፣ለእርሻ ስራ የምያገልግሉ ፣ ለአግሮ _ፕሮሰሲንግ ስራ የምያገልግሉ ስማርት ፖል … ወዘተ የተለያዩ ማሽኖችና የማሽን አካላት እንደምገኙ ሀላፍው ገልፀዎል::

በተጨማሪም እነዚህ ማሽኖችን አገር ውስጥ በማምረት ወደ ገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እንድገቡ እና የውጪ ሚንዛርን በማስቀረት አገርቷ የያዘችውን እቅድ ከዳር ለማድረስ ከፍተኛ ሚና አለው ብለዋል።

በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ማሽን አምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች እንደተናገሩት በመንግሥት በኩል የተለያዩ ድጋፎች እንደምደረግላቸው የገለጹ ስሆን ከእነዝህም ውስጥ :የደቡብ ካፒታል የልዝ ፋይናንስ ተቋሚ ለደንበኞቻቸው ከአምራቾች ማሽኖቹን መግዛት መጀመሩ ፣ በሀገራዊ እና በክልላዊ ፐሮጀክቶች የተለያዩ ትዕዛዞችን ተቀብለው በመስራት ላይ እንደምገኙ :

የመስሪያ ፣ የመሸጫና ማሳያ ቦታ ድጋፍ … የመሳሰሉ ድጋፍ እንደምደረግላቸው እና የበለጠ የተለያዩ ማሽኖች እና የማሽን አካላትን በማምረት ለክልሉ እና ለሀገራው እድገት የድርሻውን ለመወጣት መዘጋጀታቸውንና መንግሥትም አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንድቀጥል ጠይቀዋል።

ሀዋሳ|መስከረም 7/2018 ዓ .ም የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት

Scroll to Top