sbid

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሠራተኞች አድስ ከተሾሙት አመራር ጋር ትውውቅ አደረጉ።

አዲስ የተሾሙት የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበረ ከቢሮዉ ባለሙያዎች ጋር ትውውቅ አደርገዋል።

በትውውቅ መድረክ ላይ ኃላፊዉ ባስተላለፉት መልዕክት መንግሥት የሰጠውን ህዝብን የማገልገል አደራ በአንድነት ተጋግዘን በጋራ እናሳካዋለን፣ እንድሁም በሀገር ደረጃ ለኢንዱስትሪ የተሰጠው ሀላፊነት እጅግ ትልቅ ስለሆነ የማምረት አቅምም ጨምሯል ብለዋል ።

በተጨማሪ ይህን የሆነው የክልሉ መንግሥት በሰጠው ትኩረት እና የዚህ ቢሮ የጋራ ትጋት ስለሆነ ወደዚህ ቢሮ ስመደብ በሙሉ ደስታ ነው የተቀበልኩት

ይህ ደስታ ሙሉ የሚሆነው የተሰጠንን እቅድ 100% አሟልተን ስንሰራ ነው አመራሩ ዳይሬክቶሬቱ እንዲሁም ባለሙያው በተቀመጠው ፕላትፎርም መሰረት እንሰራለን በማለት መልዕክት በማስተላለፊ የዕለቱ የትውውቅ መድረክ ተጠናቋል

በትዉዉቅ መድረኩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ በቀጣይነት ዉይይት እንደሚደረግ ተገልጿል።

ሐዋሳ፣ መስከረም 27/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት

Scroll to Top