sbid

የቀድሞ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና እና አዲስ የተመደቡ ሀላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበረ ጋር ትውውቅና የስራ ርክክብ አደረጉ

አዲሱ የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ አሻግሬ ጀምበረ ቢሮ በሀላፊነት ሲመሩ ከቆዩት ከአቶ ጎሳዬ ጎዳና ጋር ትውውቅና የስራ ርክክብ አድርገዋል።

አዲሱ የቢሮ ኃላፊ ከቢሮዉ ምክትሎችና ከሌሎች ሥራ ኃላፊዎች ጋር ትዉዉቅ በማድረግ በቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ዉይይት አድርገዋል።

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባለፉት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን ግምገማ ተከትሎ አዲስ የስልጣን ምደባና ሽግሽግ ማድረጉ የሚታወስ ነዉ።

ሀዋሳ፣ መስከረም 26/2018 ዓ.ም የሲዳማ ክልል ኢ/ልማት ቢሮ የህ/ግን/ዳይረክቶሬት

Scroll to Top