sbid

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አቅም ለሌላቸው ቤተሰብ ያስገነባውን ሶስት ቤቶችን አስረክቧል።

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በምስራቃዊ ሲዳማ ዞን ቦና ወረዳ፣ በደቡባዊ ሲዳማ ዞን አለታወንዶ ከተማ አስተዳደርና ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ አቅም ለሌላቸው ቤተሰብ ያስገነባውን ሦስት ቤት በዛሬው ዕለት አስረክበዋል።

በርክክብ ስነ_ስርዓት ላይ በመገኘት መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ኢንደስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና እንደተናገሩት በክልሉ የተጀመረውን ሰው ተኮር አስተሳሰብ ተግባራዊ በማድረግ እና በመተጋገዝ ብዙ ወገኖችን ከችግር መውጣት ተችሎአል ብለዋል።

በተጨማሪም አቶ ጎሳዬ ጎዳና መተጋገዝን ባህላችን በማድረግ ይህ በጎ ተግባር እንድስፋፋ ሁላችንም የበኩላችንን ድርሻ መወጣት አለብን በማለት ለዚህ ድጋፍ የቢሮው አመራሮች፤ ሰራተኞችና የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርቧል።

ቢሮው አቅም ለሌላቸው ቤተሰብ ገንብቶ ያስረከበው ሶስት ቤቶች በብርና በዓይነት ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት መሆኑን ተነግሯል።

የክልሉ የሴቶች፣ ወጣቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ እመቤት ኢሳያስ እንደተናገሩት ይህ የቤጎ ፍቃድ ስራ በክልላችን የተቸገሩ አቅም የሌላቸውን ቤተሰብ ለመርዳት የተጀመረው ስራ ጠንካራ በመሆኑ ቤትን ገንብቶ መስጠት እየተስፋፋ ነው ያሉት ኃላፊዋ ይህ ተግባር ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ገልፀው ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ እነዚህ ቤተሰቦችን ለመርዳት ላደረጉት አስተዋጽኦ ከፍ ያለ ምስጋና አቅርቧል።

በቢሮው ድጋፍ የተረገላቸው ቤተሰቦች እንደተናገሩት ከዚህ በፊት ደረጃውን የጠበቀ መጠለያ ስለለላቸው ዝናብና ፀሐይ እየተፈራረቀባቸው ችግር ውስጥ መቆየታቸውን ገልፀው ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርቧል።

የተገነቡ ቤቶች ቁልፍ ከማስረከብ ስነስርዓት በተጨማር ሶስቱም ቤተሰቦች በዘለቀታ ቋሚ ገብ አግኝተው እራሳቸውን እንድችሉ በፍላጎቶቻቸው መሠረት የተለያያዩ ግብዓቶች የተሰጣቸው ስሆን በመርሀ_ግብሩ ላይ የቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች የክልሉ የሴቶችና የወጣቶች ማሕበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ኃላፍዎች ኢንዲሁም የወረዳና ከከተማ አስተዳደር አመራሮች ተገኝተዋል።

   ===================

ሰኔ 28/2017 ዓ .ም

የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት

Scroll to Top