sbid

በክልሉ የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም 63.2 በመቶ ማድረስ ተችሏል አቶ አሻግሬ ጀንበሬ።

የካቲት 9/2018 የሲዳማ ክልል ኢ/ል/ቢሮ የኮሙኒኬሽን ዳይሮክቶሬት

በበጀት አመቱ በስድስት ወራት የስራ አፈጻጸም የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም 63.2 በመቶ ማድረስ መቻሉን የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ ተናግረዋል።

የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ተገኝተው የዞን አመራሮች፣ የወረዳና የዘርፉ አመራሮች አንዲሁም ባለድርሻዎች በተገኙበት የስድስት ወራት አፈጻጸምና ግብረ መልስ የውይይት መድረክ አካሂደዋል።

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሻግሬ ጀንበሬ በክልሉ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን ለማሳደግ ሰፊ ስራ መሰራቱን ተናግሮ በበጀት አመቱ በስድስት ወራት የአምራች ኢንዱስትሪዎች አማካይ የማምረት አቅም አጠቃቀም 63.2 በቶ ማድረስ መቻሉን ተናግረዋል።

በመቀጠልም በተያዘው በጀት አመት የገጠር ኢንዱስትሪዎችን በማስፋፋት ጥሩ የገበያ ትስስር በመፍጠር ፍልሰትን ለማስቆምና የስራ ዕድል ለመፍጠር በማለም አንዲሁም ኤክስፖርት አቅምን ለመጨመር ከባለድርሻ አካላት በመቀናጀት እየተሰራ በመሆኑ አንስተዋል።

የሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጻድቁ ባጥሶ እንደተናገሩት መንግሥታችን በዘርፉ በሰጠው ትልቅ ትኩረት አመርቂ ውጤት እየተገኘ መሆኑን ተናግሮ አንድ ሀገር የእድገት መሰረቱ ኢንዱስትሪ በመሆኑ ያሉንን ዕድሎች አሟጠን መጠቀም አለብን በማለት ተናግሯል።

በመጨረሻም የውይይት መድረክ ላይ የክልሉ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አመራሮች የሰሜናዊ ሲዳማ ዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም የኢንደስትሪ ልማት ጽ/ቤቶች እና የሚመለከታቸው አካላት ታድመዋል።

Scroll to Top