sbid

የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ማስፋፋትና ማበረታታት እንዴ ክልል የአማራጭ ጉዳይ ሳይሆን የግዴታ ነው አቶ በየነ ባራሳ።

የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ ማስፋፋትና ማበረታታት እንዴ ክልል የአማራጭ ጉዳይ ሳይሆን የግዴታ ነው ስሉ የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ እና የኢንዱስትሪ ልማት ምክር ቤት ዋና ሰብሳብ አቶ በየነ ባራሳ ተናግረዋል።

የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ያካሄዱ ስሆን በመድረኩ የኢንዱስትሪ ምክር ቤት የ2017 በጀት አመት የስራ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት አመት መሪ እቅድ አቅርቦ ውይይት በማድረግ በምክር ቤት አጽድቋል።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ የኢንዱስትሪ ልማት ምክር ቤት ዋና ሰብሳብ አቶ በየነ ባራሳ ኢንዱስትሪ ለአገር ኢኮኖሚ ዋልታ ነው ከፍተኛ የሰው የስራ ዕድል እንዲያገኙ የሚያስችል አንዲሁም የውጭ አገር ምንዛሬ በማስቀረት በአገር ውስጥ ግብዓት እንድተኩ ለማድረግ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለዚህ የባለድርሻ አካላት ቅንጅት ከሌለ የኢንዱስትሪ ልማት ስራ ውጤታማ ልሆን አይችልም በማለት ተናግረዋል።

በመቀጠል ክልላችን ጠባብ የመሬት ቆዳ ስፋት ያለበት በመሆኑ የኢንደስትሪ ልማት ዘርፍን ማስፋፋት እና ማበረታታት የአማራጭ ጉዳይ ልሆን አይችልም የግዴታ ነው ያሉ ስሆን ዘርፉን የበለጠ ውጤታማ እንዲሆን ማጠናከር ይጠበቅብናል ብለዋል።

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና በመድረኩ እንደተናገሩት ኢንዱስትሪ የሚያመርተውን ምርት ጥራት እንድኖረው እና አለም አቀፍ ተወዳዳሪ እንድሆኑ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ በመሆኑ ለዚህም የባለድርሻ አካላት ሚና የጎላ ስለሆነ ሁሉም የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክሮ እንድቀጥል በማለት ተናግሯል።

በመጨረሻም የኢንዱስትሪ ልማት ምክር ቤት አባላት ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በ2017 የታዩ ጉድለቶችን በማረም ለ2018 በጀት አመት በተግባር የታጀበ ውጤት ለማስመዝገብ እንሰራለን ብለዋል።

መስከረም 16/2018 ሲዳማ /ክ/ኢ/ልማት ቢሮ ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተሮት

Scroll to Top