sbid

የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፣ሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ''በመትከል ማንሰራራት'' በሚል መሪ ቃል የአረንጓዴ አሻራ (ችግኝ ተከላ) መርሃ-ግብር አካሄደ

የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ፣ሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ የአረንጓዴ አሻራ (ችግኝ ተከላ) መርሃ-ግብር አካሂደዋል።

በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ (በአሁኑ ስያሜ ሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን) ግቢ ችግኝ ተከላ የተካሄደ ሲሆን መርሃ ግብሩን አስመልክተው የሶስቱም ተቋማት ኃላፊዎች ባደረጉት ንግግር ሀገራችን በያዘችው ልማት ጎዳና አሩንጋዴ አሻራ ለሁሉም ልማት መሠረት ከመሆኑ ባሻገር የሰው ልጅ በህይወት ለመኖር ወሳኝ በመሆኑ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ስተገበር መቆየቱን አስገንዝበዋል።

በመርሃ ግብሩ የሲዳማ ክልል የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጎሳዬ ጎዳና፣ሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ስራ አስኪያጅ አቶ ማቴዎስ አሸናፊ፣የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ኃይሉ ዬተራ፣የሀዋሳ ልዩ ኢኮኖሚ ዞን ሠራተኞች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተው ተሳትፈዋል።

ሐምሌ 18/2017 ዓ.ም

የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ  የህ/ጉን/ዳይ/ዳይሮክቶሬት

Scroll to Top