የሲዳማ ክልል ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም የላቀ ውጤት በማስመዝገብ በአገር አቀፍ ደረጃ ለአራት ተከታታይ ዓመት ተሸላም ሆነ፡፡
የኢፌዴሪ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ የሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደር የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፍዎችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ሲያካሂድ የቆዬ ሲሆን በአመቱ አፈፃፀም መነሻ በተደረገው ምዘና ቢሮአችን ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት ጋር ተወዳድሮ ከአዲስ አበባ ከተማ እና ከኦሮሚያ ክልል በመቀጠል ሦስተኛ ደረጃ በመውጣት ለቢሮ አገልግሎት የሚሆን ቁሳቁስ፣የዋንጫ እና መዳሊያ ተሸላም ሆኖአል።
በመሆኑ ዘርፉን ስትደግፉ የነበራችሁ አመራሮች ፤ባለሙያዎች፤ የኢንዱስትሪ ባለበቶች ፤ባለድርሻ አካላት እንድሁም መላው የሲዳማ ክልል ነዋሪዎች ውጤቱ የጋራ ልፋት ውጤት በመሆኑ እንኳን ደስ አለን /አላችሁ እያለን
ሽልማቱ ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያነሳሳ በመሆኑ በ2018 በጀት ዓመት እጅ ለእጅ ተያይዘን ከዝህ የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ ከዝህ በበለጠ ህዝባችንን ተጠቃም ለማድረግ በጋር እንድንረባረብ ቢሮው ጥሪውን ያቀርባል።